ለብዙ በሽታዎች መተላለፊያ ምክንያት የሆነው እጅ መጨባበጥ ዘመኑ እያለቀበት ነው፡፡

ምን እነደ ጦጣ እጁን ትዘረጋብኛለህ ሲሉ የነበሩ አረጋውያን ተስፋ ቆርጠው ዝም ባሉበት ወቅት ወይም እድሜ እያቋረጣቸው እየቀነሱ ባሉበት ዘመን እጅ መጨባበጥና ባልታጠበ እጅ አይንን፣ አፍንጫንና አፍን መነካካት የ ኮሮና ቫይረስ ዋና መተላለፊያ  መሆኑ መታወቁ ባልታሰበ ጊዜ ይህን መጤ ባህል እርግፍ አድርገን እንድንተው ያስገድደናል፡፡

 

የኛ ባህል እጅ መንሳት ዎይም ጎንበስ ብሎ ሰላምታ የሚሰጠውን ሰው ማክበር እንጅ እጅን መዘርጋት የስድብ ያህል ይቆጠር ነበር፡፡ አሁን ባለንበት ዘመን ግን ጭራሽ የኛ ባህል እንደሆ ተደርጎ ከመጨባበጥ አልፎ ትክሻ ለትክሻ መጋጭት፣ በደረት መላተም እያደገና በየትውለወዱ ዘርፍ እያወጣ መጥቷል፡፡

አበው እጅ መጨባበጥ በሀገራችን ሲጀመር “ጨብጥና መጨባበጥ  የጨካኙ እና የወራሪው የሰላቶ ነው”  በማለት ለማስቆም ሞክረው ነበር

; በኋላ ከዘመናዊ  ትምህርት ጋር ተዋዝቶ ሀገሪቱን እንደገና ቢያጥለቀልቃትም፡፡

ደህና ሰንብት መጨባበጥ

ሹልክ ብለህ አንደገባህ ሹልክ ብለህ ውጣ! እኛ ወደ ጤነኛው፣ ወደ ንጹሁ፣ ክብርና ሞገስ ወዳለው የሠላምታ ስነስርዓታችን እንመለስ፡፡ ከመቀመጫችን ብድግ ብለን ጤና ይስጥልኝ እንባባል፡፡ አዲስ ነገር ሁሌ ባይመችም ጥቂት ከተለማመድን በዙሪያችንን ያሉ ሰዎቸ እዲተገብሩት ካበረታታን ወደ መሰረታቸን መመለስ ይህን ያህል አይከብድም፡፡

የኛ ኢፊሴላዊ ሰላታ እጅ መንሳት ነው፣ ማክብር መከበር ስለሆነ ክብራና ሞገስ አለው !

ጤና ለሚያሳጣን መጤ ባህል ይህን ያህል መጨነቅ አያስፈልግም፣ በይሉኝታ መተብተብም አያስፈልግም!!

እጅ ባለመጨባበጥ፣ አዘዉትሮ እጅን በውሀ እና በሳሙና በመታጠብ፣ አይንን ፣አፍንጫንና አፍን ባለመነካካት በርካታ ተላላፊ በሽታዎችን መከላከል ይችላሉ ለምሳሌ፡፡

  • ጉንፋን
  • ኢንፍሎይንዛ
  • የወቅቱን ኮቪድ-19
  • የአይን በሽታ (አይን ማዝ/ትራኮማ፣ ኮንጃክቲቲቫይትስ)
  • የቆዳ በሽታ (እከክ፣ ጭርት፣ማዲያት በፈንገስ ምክንያት የሚመጡ የተለያዩ በሽታዎች)
  • ቡግንጅ፣ ሌሎች መግል የሚያስከትሉ በሽታዎች (ስታፊሎ ኮከስ በሚባል ባክቴሪያ)
  • ቁርባ (በተለይም የቆዳ/ኩታንየስ አንትራክስ የሚባለው)
  • የተቅማጥ በሽታ (ኮሌራ፣ ዴዘንትሪ፣ ታይፎይድ የመሳሰሉትን ጨምሮ በርካታ በቫይረስና በባክቴሪያ ሚመጡ በሽታዎችን ያካትታል)
  • የሆድ ጥገኛ ትላትሎችን (አሜባ፣ ወስፋት…)
  • የጉበት በሽታ (በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣው ሄፓታይትስ ኤ)
  • በግብረስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች አብዛኞቹ በመጨባበጥ እና በሌሎች አይነት የሰውነት ንክኪ ይተላለፈሉ ( ጨብጥ፣ ቂጥኝ፣ ባምቡሌ፣ ዋርት/ፓፒሎማ ቫይረስ ሲከፋ የማህጸን ጫፍ ካንሰር የሚያመጣው …)

እንደዚህ ቀላል በሆነ ነገር ስንታመስ መኖራችን ያሳዝናል፣ ሁንም አረፈደም፡፡ ኮቪዲ 19 ቢኖረም ባይኖርም ልማድ ልናደርገው የሚጋባ የኛ የራሳችን የተሸለ ባህል ነው፡፡

የሚያውቅ ብቻ ሳይሆን የሚፈጽም ይድናል !!! ተግቶ የሚለማመድ ሰው የሚደነቅበት ባህሪው ያደርገዋል!

ጤና እና ክብር ለሁላችን !!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may also like

No announcement available or all announcement expired.