5. የጫማ ማሰሪያዎችን በትክክል ሣያስሩ ደረጃዎችን መውጣትና መውረድ፡- የተፈታውን የጫማ ማሰሪያ በሌላኛው እግር በአጋጣሚ ከተረገጠ ወይም የሆነ ነገር ገያዘው ወደፊት በማደናቀፍ የከፋ አደጋ ያስከትላል፡- በተለይ ይህ ጉዳይ ደረጃ በሚወርዱበት ወቅት ከተከሠተ ወደፊት ስለሚያፈናጥር እጅ፣ የወገብ የአንገት፣ የጥርስና የጨንቅላት አጥንት ስብራት ሊያስከትል ይችላል፡፡ ጭንቅላት በሚመታበት ወቅት ወደውስጥ ደም ሊፈስ ስለሚች ለሞት ያደርሳል፡፡

   

6. በደረጃዎችና በመተላለፊያ ቦታዎች አላስፈላጊ ጨዋታ ማለትም ቀልድና መላፋት ወይም መራገጥ ፈረንጆቱ Horse play የሚሉት አይነት እንዲሁም በደረጃ መወጣጫዎች ላይ መንጠላጠል ሰውነት ጥሎ መውጣትና መውረድ፡- ይህ ሁኔታ በትምህርት ቤቶችና ወጣቶች አዘውትረው በሚገኙባቸው ቦታዎች በብዛት ይታያል፡፡

7. በደረጃዎች አቅምን ባላገናዘበ ሁኔታ ከባድ እቃ ተሸክሞ ለመውጣት/ ለመውረድ መሞከር፡- መሬት ላይ ቻልነው ማለት ደረጃ ላይ ይዘነው እንወረዳለን/እንወጣለን ማለት አይደለም፡፡

8. የሚያንሽራትቱ፣ ሶላቸው ያለቀ ወይም የለሠለሰ ጫማወችን መጠቀም፡- አንዳንድ የቤት ውስጥ ጫማወች የከፋ አደጋ ያጋልጣሉና በምንገዛበት ጊዜ ይህን ያገናዘበ መሆን አለበት፡፡


9. ረዥምና የሚጎተቱ ልብሶችን ለብሶ ደረጃ ለመውጣት/ለመውረድ መሞከር፡- ረዥም ቀሚስ/ቢጃማ የሚያዘወትሩ ሴቶች፣ ነጠላ/ጋቢ የሚያደረጉ እናቶችና አባቶች ለዚህ አደጋ የተጋለጡ ናቸው፡፡ የሚጎተት ልብሳቸውን ጫፍ ራሣቸው ወይም ሌላ ሰው በሚረግጥበት ጊዜ ወይም የሆነ ነገር ሲይዘው አደነቃቅፎ ወይም ሚዛናቸውን አስቶ ይጥላቸዋል፡፡

10. በሀሣብ ተወጥሮ ወይም በጨዋታ ውሥጥ ሆኖ፣ ወይም ጥሞና የሚያስፈልገውን ከፍተኛ ጉዳይ በስልክ እየተወያዩ ደረጃዎችን ለመውረድ መሞከር፡- አንዳንደ ሰዎች በጆሮ ማዳመጫ ተመስጠው እያወሩ እጃቸውን ከኪሣተው ከተው ደረጃ ሲወርዱ ይታያሉ፡፡

  

ደረጃ በመውጣት ጊዜ ከሚከሰት አደጋ ይልቅ ደረጃ በሚወርዱበት ጊዜ የሚከሰተው የከፋና የበዛ ነው፡፡ ተጨማሪ ወይም ሰው ጠጠንቅቆ ከአደጋ የሚድንብት ልምድና ሀሣብ ካለዎ ይጻፉልን፡፡ ሁኔታዎች ሲለዎጡ አኗኗራችን አብረን እናስተካክል እንማማር!!!

አንድም ሠው ያላሠበው አደጋ አይድረስበት አሜን !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may also like

No announcement available or all announcement expired.