የኋላ ቀርነት ማህተም/ የተተፋ መስቲካ/ Chewing gum and the city

በፋሲል ፀጋዬ 

በየዩኒቨርሰቲው ባለእጅ መደገፊያ ወንበሮች፣ በየመጽሀፍት ቤቱ፣ በየካፌቴሪያው ጠረጴዛ የውስጠኛው ክፍል ተሳስታችሁ ጉልበታችሁን ካስጠጋችሁ ልብሣችሁ በርካታ የመስቲካ ልጥፎችን የዞ ይመለሣል፡፡ በዚህ ጉዳይ ብዙ ሰው ሲማረር እሠማለሁ የደረሰባችሁ ካላችሁ አስተያየታችሁን ጻፉልን ወይም በድምጽ መልእክት አድርሱን፡፡

በእምነበረድ ባጌጡ  ደረጃዎች፣ የሚያብረቀርቁ የህነጻ ውስጥ መተላለፊያ ቦታዎች፣ የስብሰባ አዳራሾች  ውስጥ አፋቸውን ከፍተው መስቲካ የሚለጥፉ ሰዎች እጅግ ይገርማሉ፡፡ በአዳዲሶቹ የአዲስ አበባ ክ/ከተሞች ህንጻዎች ገና ከመከፈታቸው ከእምነበረዱና ከሸክላ ንጣፉ ውበት ይልቅ የተለጠፈባቸው የመስቲካ አሻራ ደምቆ ይታያል፡፡

አለማዎቅ እነዳይባል ዩኒቨርስቲዎችም ችግሩ የባሠባቸው ናቸው፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ደረጃዎች፣ ፒያሣ የሚገኘው አራዳ ህንፃማ ደረጃው በተተፋ መስቲካ ተለጣጠፎ ብል የበላው የአነር ቆዳ መስሏል፡፡ አነዲያ ንጹህና ያማረ ቦታ ላይ ያኘኩትን መስቲካ የሚጥሉ ሠዎች እቤታቸው ሳሎን ወይም መኝታ አንሶላቸው ላይ መስቲካ እንደማይለጥፉ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ ለይተው የሚያደረጉ ከሆነ ደግሞ እያወቁ ነው ማለት ነው ፡፡ ይህን ብቻ አይቶ የወጣቶቻችን የስልጣኔ ደረጃ፣ ለጋራ መጠቀሚያ ቦታዎችና ለሚጠቀሙበት ቁሣቁሥ የሚሠጡትን ትኩረትና የሚዎስዱትን  የወረደ የሃላፊነት ስሜት ያሣብቅባቸዋል፡፡

የህዝብ ስልጣኔና ልዕልና የሚታየው በጋራ መጠቀሚያ ቦታዎች አያያዝና ንጽሕና እንጅ በያንዳንዱ ጓዳ ጎድጓዳ አይደለም ፡፡ የከተሞች ውበት ሲነሳ የመንገዶች ጽዳት፣ የፓርኮች ብዛትና ውበት፣ የአደባባዮቻቸው አያያዝ፣ የግረኛ መንገዶቻቸው ጽዳትና ምቾት እንጅ የየ አንዳንዱ ሠው ሳሎን ጽዳትና ውበት አይደለም፡፡ እያዳንዱ ዜጋ በዘፈቀደ ባይጠል በየቦታው ባይጸዳዳ፣ ባይተፋ  ንጹህ ከተማ ሊኖረን እንደሚችል ግልጽ ነው ፤ ከተማ ባለመጣል እነጅ በማጽዳት ንጹህ አይሆንም፡፡

በአብዛኛው ሰልጥነዋል በሚባሉ ሀገራት እንኳንስ በደረጃዎችና በህንጻ ውስጥ ይቅርና በጫካ ወስጥ መስቲካ ሰትተፉ የኪስ ሶፍት ጨምሮ የጠጣችሁበትን የውሃ ላስቲክ ስትጠሉ ብትታዩ እያንዳንዱ ዜጋ በማነዎር ብቻ አያልፋውም ከተቆጣጣሪው አካልም ከፍተኛ ቅጣት ይከተላችኋል ፡፡ ሲጀመር ሁሉም ራሱን ያከብራልና እንዲህ አይነት አስነዋሪ ተግባር የሚፈጽም ሠው ብዙም አይታይም፡፡

ለምሣሌ ለህክምና አገልግሎት ካልሆነ በስተቀር ወደ ሲንጋፖር ምንም አይነት ማስቲካ አይገባም እዛውም አይመረትም፡፡ ያለህክምና ፈቃድ መስቲካ በማንኛውም ቦታ አይሸጥም መስቲካ  ማኘክም ክልክል ነው ፡፡ አንድ ሠው ሲንጋፖር ውስጥ መስቲካ ሲያኝክ / ሲተፋ ከተገኘ $700/ሰባት መቶ የአሜሪካን ዶላር ወይም አሁን ባለው ምንዛሬ ከ 15,000.00/ከአስራ አምስት ሽህ ብር በላይ ይቆነደዳል፡፡ እንግዲህ ይህ የህዝብ ስልጣኔና የቁጥጥር ስርዓት ነው ሲንጋፖርን የምታማልል ንጹህ፣ በሚሊዮኖች የምትጎበኝ የስልጡኖች ከተማ እነድትሆን  ያበቃት፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may also like

No announcement available or all announcement expired.